ኢዮብ 20:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሀብቱ ትርፍ የለውም፤ ስለዚህ በረከቱ አትከናወንለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለውን አሟጥጦ ስለሚበላ፣ ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥ ስለዚህ በረከቱም አይጸናም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብቱ ሁሉ ተሟጦ ስለሚያልቅ የሚቀምሰው ነገር አያገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥ ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም። |
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
ይህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰምቶአልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆናሉ፤ ታላላቅና የሚያምሩ ቤቶችም የሚቀመጥባቸው አይኖርም።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአለው ዙሪያሽ ድረስ ምድርሽ ይጠፋል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፤ ሀገሮችሽም ይበዘበዛሉ።”