ኢዮብ 19:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌን ማን በጻፈው! ማንስ በመጽሐፍ ውስጥ ለዘለዓለም ባተመው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ! በመጽሐፍም በታተመ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምነው አሁን ቃሌ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ውስጥ ቢታተም! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስከ አሁን የተናገርኩትን ቃል የሚያስታውስና በመጽሐፍ የሚመዘግበው ሰው ቢገኝ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምነው አሁን ቃሌ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ውስጥ ቢታተም! |
የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ!
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።