ኢዮብ 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስብም ፊቱን ከድኖአልና ስቡንም በወገቡ ላይ አድርጎአልና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፊቱ በስብ ቢሸፈን፣ ሽንጡ በሥጋ ቢደነድንም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስብም ፊቱን ከድኖአልና፥ በውፍረትም ወገቡ ተሸፍኗልና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊቱ በስብ ተሸፍኖአል ወገቡም በውፍረት ተድቦልብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስብም ፊቱን ከድኖአልና፥ ስቡንም በወገቡ ላይ አድርጓልና፥ |
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።