ጥንቱን ዕውቀትንና ምክርን የሚያስተምር እግዚአብሔር አይደለምን? በነፍሰ ገዳዩስ የሚፈርድ እርሱ አይደለምን?
ኢዮብ 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማይም በፊቱ ንጹሕ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ቅዱሳኑን እንኳን አያምናቸውም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በመላእክቱ ላይ እምነት የለውም፤ ሰማያት እንኳ በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፥ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። |
ጥንቱን ዕውቀትንና ምክርን የሚያስተምር እግዚአብሔር አይደለምን? በነፍሰ ገዳዩስ የሚፈርድ እርሱ አይደለምን?