መተላለፌን በከረጢት ውስጥ አትመሃል፥ ኀጢአቴንም ለብጠህባታል።
መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።
መተላላፌን በከረጢት ውስጥ ታትሞ፥ ኃጢአቴንም በለበጥህበት ነበር።”
በከረጢት ታሽጎ እንደሚወረወር ጒድፍ በደሌን ሁሉ ታስወግድልኛለህ ኃጢአቴንም ትደመስስልኛለህ።
መተላልፌ በከረጢት ውስጥ ታትሞአል፥ ኃጢአቴንም ለብጠህበታል።
ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥ ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፤
ልጆቹ ሀብቱን አያገኙም። እግዚአብሔር ብድራቱን ይከፍለዋል። እርሱም ያንጊዜ ያውቃል።
እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አልበደልሁምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢአትንም አልሠራሁም።
ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፤ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።
በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፤ ልብሴም ይጸየፈኛል።
በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙና ብታበዢ፥ በእኔ ፊት በኀጢአትሽ ረክሰሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የውሉንም ወረቀት ጻፍሁ፤ አተምሁትም፤ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።
የዐመፅህን ወንጀል ታገሥሁት፤ የኤፍሬም ኀጢአቱም ተከማችትዋል ።
ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ ሐረጋቸውም ከገሞራ ነው፤ ፍሬአቸውም ሐሞት ነው፤ ዘለላቸውም መራራ ነው።
በእኔ ዘንድ ያለው ትእዛዝ ይህ አይደለምን? በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?