በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም።
ኢዮብ 12:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይፍገመገማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርሃን በሌለበት ጨለማ በዳበሳ ይሄዳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንም በሌለበት ጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ያቅበዘብዛቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃን አጥተው በጨለማ እንዲደናበሩና እንደ ሰከረም ሰው እንዲንገዳገዱ ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ይቅበዘበዛሉ። |
በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም።
እግዚአብሔር የሚያስት መንፈስን ልኮባቸዋልና፤ ሰካርም፥ ደም ያዞረውም እንዲስት እንዲሁ ግብፃውያን በሥራቸው ሁሉ ሳቱ።
ምድር በወይን እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ ሕግን መተላለፍዋም ይከብድባታል፤ ትወድቅማለች፤ ደግማም አትነሣም።
እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመሱ፤ ዐይንም እንደሌላቸው ተርመሰመሱ፤ በቀትርም ጊዜ በመንፈቀ ሌሊት እንዳለ ሰው ተሰናከሉ፤ እንደ ሙታንም ይጨነቃሉ።
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።
ዕውር በጨለማ እንደሚዳብስ በቀትር ጊዜ ትዳብሳለህ፤ መንገድህም የቀና አይሆንም፤ በዘመንህም ሁሉ የተገፋህ፥ የተዘረፍህም ትሆናለህ፤ የሚረዳህም የለም።