በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚህም እርሻ እበቀለዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።”
ኢዮብ 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአለቆች ላይ ውርደትን ያመጣል፥ ትሑታንንም ያድናቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥ የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መኳንንትን ያሳፍራቸዋል፤ የኀያላንን ኀይል ያስወግዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥ የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል። |
በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚህም እርሻ እበቀለዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።”
መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፤ አክሊልህንም እሰጠዋለሁ፤ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩና በይሁዳም ለሚኖሩ አባት ይሆናል።
በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም ሀገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
እግዚአብሔር አምላክ ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦
አይራቡም፤ አይጠሙምም፤ አይደክሙም፤ አይተኙም፤ የወገባቸውን መታጠቂያ አይፈቱም፤ የጫማቸውም ማዘቢያ አይበጠስም።