ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
ኢሳይያስ 44:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መተላለፍህን እንደ ደመና፥ ኀጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥችሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መተላለፍህን እንደ ደመና፣ ኀጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ ጠርጌ አስወግጃለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መተላለፍህን እንደ ደመና፥ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደልህን እንደ ደመና ኃጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ አስወግጄአለሁ፤ ስለ አዳንኩህ ወደ እኔ ተመለስ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መተላለፍህን እንደ ደመና፥ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፥ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ። |
ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል በዚህ ስፍራ የሚጸልዩትን ልመና ስማ፤ በተዘጋጀው በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥ በጻድቃንህም ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን ተስፋ አደርጋለሁ።
ዮቶርም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ እንደ አዳናቸው ሰምቶ በሁሉ አደነቀ።
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቍጥር ጥቂት የነበርህ እስራኤል ሆይ፥ እኔ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተቤዥችሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ ወደ ጽዮንም በደስታና በሐሤት ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ክብር በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፤ ኀዘንና ልቅሶም ይወገዳሉ።
ክፉ ሰው መንገዱን፥ በደለኛም ዐሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፤ እርሱም ይምረዋል፤ እርሱ ብዙ በደላችሁን ይተውላችኋልና።
አንተ ግን አቤቱ! ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውንም ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፤ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።”
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
እኔንም ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ እኔም የበደሉኝንና ያመፁብኝን ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።
በዚያ ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነዚህን በምድር የተረፉትን ይቅር እላቸዋለሁና የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አይኖርምም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፥ ምንም አይገኝም።
ታስቢ ዘንድ፥ ታፍሪም ዘንድ፥ ደግሞም ስላደረግሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍረትሽ አፍሽን ትከፍቺ ዘንድ አይቻልሽም፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው።
ሰማያት ሁሉ በአንድነት ደስ ይላቸዋል፤ የእግዚአብሔርም መላእክት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ከሕዝቡ ጋር ደስ ይላቸዋል። የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤ የልጆቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ለሚጠላቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋልና፥ እግዚአብሔርም የሕዝቡን ምድር ያነጻል።”