ኢሳይያስ 44:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠራቢውም እንጨት ቈርጦ በልኩ ያቆመዋል፤ በማጣበቂያም ያያይዘዋል፤ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል፤ በቤትም ውስጥ ያቆመዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእጅ ጥበብ ባለሙያ በገመድ ይለካል፤ በጠመኔ ንድፍ ያወጣል፤ በመሮ ይቀርጸዋል፤ በጸርከል ምልክት ያደርግበታል። በሰው አምሳል ይቀርጸዋል፤ የሰውንም ውበት ያለብሰዋል፤ በማምለኪያም ስፍራ ያስቀምጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አናጢ በእንጨቱ ላይ መስመርን ያሰምራል፤ ንድፍም ይነድፋል፤ በመላጊያ ያለሰልሰዋል፤ በማስተካከያ መሣሪያም ትክክልነቱን ያረጋግጣል፤ ውበት ያለው የሰው ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚያም በጣዖት ቤት ያኖረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠራቢውም ገመድ ይዘረጋል በበረቅም ያመለክተዋል በመቅረጫም ይቀርጸዋል በመለኪያም ይለከዋል፥ በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ያስመስለዋል። |
ያዕቆብም አለ፥ “አምላኮችህን የምታገኝበት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገንዘብህም በእኔ ዘንድ ካለ በወንድሞቻችን ፊት እይ፤ ለአንተም ውሰደው” አለ። ያዕቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረቀቻቸው አያውቅም ነበርና።
ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “ከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶች አማልክትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ ልብሳችሁንም እጠቡ፤
አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፤ ስለ ማጣበቅ ሥራውም፥ “መልካም ነው” አለ፤ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው።
እኔም ገባሁና፥ እነሆ በግንቡ ዙሪያ ላይ የተንቀሳቃሾች አዕዋፍና እንስሳትን ምሳሌ ከንቱና ርኩስ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተሥለው አየሁ።
በፊታቸውም ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎችና የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያንዳንዱ በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በስውር እያንዳንዱ በሥዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና” አለኝ።
እንግዲህ እኛ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆን በሰው ዕውቀትና ብልሀት በተቀረጸ በድንጋይና በብር፥ በወርቅም አምላክነቱን ልንመስለው አይገባም።
የማይሞተውን የእግዚአብሔርን ክብር በሚሞት ሰውና በዎፎች፥ አራት እግር ባላቸውም፥ በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።
በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትንም፥ የማይበሉትንም፥ የማያሸቱትንም፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ሌሎች አማልክት ታመልካላችሁ።
እርሱም፥ “የሠራኋቸውን አማልክቴን፥ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፤ ለእኔ ምን ተዋችሁልኝ? እናንተስ፦ ለምን ትጮኻለህ እንዴት ትሉኛላችሁ?” አለ።