La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 29:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሊባ​ኖስ እንደ ፍሬ​ያማ እርሻ ሊለ​ወጥ፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈ​ጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይ​ይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቆጠር ጥቂት ዘመን ቀርቶት የለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሊባኖስ ጫካ የእርሻ ቦታ ይሆናል፤ የእርሻው ቦታ ወደ ጫካነት ይለወጣል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቆጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይደለምን?

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 29:17
24 Referencias Cruzadas  

አንተ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተመ​ለ​ስ​ልን፥ አድ​ነ​ንም፤ ሕዝ​ብ​ህም በአ​ንተ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ይህም፥ መን​ፈስ ከላይ እስ​ኪ​መ​ጣ​ላ​ችሁ፥ ምድረ በዳ​ውም ፍሬ​ያማ እርሻ እስ​ኪ​ሆን፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ ዱር ተብሎ እስ​ኪ​ቈ​ጠር ድረስ ይሆ​ናል።


በም​ድረ በዳ ዝግ​ባ​ው​ንና ግራ​ሩን፥ ባር​ሰ​ነ​ቱ​ንና የዘ​ይ​ቱን ዛፍ አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


በእ​ሾ​ህም ፋንታ ጥድ፥ በኵ​ር​ን​ች​ትም ፋንታ ባር​ሰ​ነት ይበ​ቅ​ላል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በማ​ይ​ጠፋ ምል​ክት ይመ​ሰ​ገ​ናል።


በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራህ ከር​ስ​ትህ ጥቂት ክፍል እና​ገኝ ዘንድ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያለ ንጉ​ሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥ​ዋ​ዕ​ትና ያለ ምሥ​ዋዕ፤ ያለ ካህ​ንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉ​ድና ያለ ተራ​ፊም ብዙ ወራት ይቀ​መ​ጣ​ሉና፤


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ገና አንድ ጊዜ በቅርብ ዘመን እኔ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስንም አናውጣለሁ፣


ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች፤ ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።


“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።