እነርሱ ግን ዐመፁብኝ፤ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ አላስወገደም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ በግብፅ ምድር መካከል ቍጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ሕዝቅኤል 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ግባ፤ በዚህ የሚያደርጉትን ክፉውን ርኵሰት እይ” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ግባና በዚህ የሚፈጽሙትን እጅግ የከፋ ርኩሰት ተመልከት አለኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ግባ፥ በዚህ የሚያደርጉትንም ክፉውን ርኩሰት ተመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚያ የሚያደርጉትን ክፉና አጸያፊ ነገር ተመልከት!” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ግባ፥ በዚህም የሚያደርጉትን ክፉውን ርኵሰት እይ አለኝ። |
እነርሱ ግን ዐመፁብኝ፤ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ አላስወገደም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ በግብፅ ምድር መካከል ቍጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
እኔም ገባሁና፥ እነሆ በግንቡ ዙሪያ ላይ የተንቀሳቃሾች አዕዋፍና እንስሳትን ምሳሌ ከንቱና ርኩስ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተሥለው አየሁ።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚያደርጉትን ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን፥ ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ” አለኝ።