እነሆ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፤ በግብፅም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
ሕዝቅኤል 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍጻሜ መጥቶአል፤ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ነቅቶብሻል፤ እነሆ ደርሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጻሜ መጥቷል! ፍጻሜ መጥቷል! በአንቺ ላይ ተነሣሥቷል፤ እነሆ፤ ደርሷል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጻሜ መጥቷል፥ ፍጻሜ መጥቷል፥ በአንቺ ላይ ነቅቷል፥ እነሆ፥ መጥቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጨረሻው መጥቶአል፤ መጨረሻው ደርሶአል፤ በእናንተ ላይ ተነሥቶአል፤ እነሆ፥ መጥቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍጻሜ መጥቶአል፥ ፍጻሜ መጥቶአል፥ ነቅቶብሻል፥ እነሆ፥ ደርሶአል። |
እነሆ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፤ በግብፅም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
ጻዴ። ልጆቻችንን ወደ አደባባያችን እንዳይወጡ ከለከልን፤ የምንጠፋበት ጊዜ ደርሷልና ዘመናችን አለቀ፤ የምንጠፋበትም ጊዜ ቀረበ።
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ፤ በእስራኤልም ዘንድ ደግሞ ምሳሌ አድርገው አይናገሩትም፤ አንተ ግን፦ ዘመኑና የራእዩ ሁሉ ነገር ቀርቦአል በላቸው።
“እነሆ ቀኑ ደርሶአል፤ እነሆ! የእግዚአብሔር ቀን ወጥታለች፤ ስብራትህ ደርሶአል፤ ብትርም አብባለች፤ ስድብም በዝቶአል።
አሁንም ፍጻሜ በአንቺ ላይ ደርሶአል። ቍጣዬንም እሰድድብሻለሁ፤ እንደ መንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፤ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ።
እርሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው” አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።