ሕዝቅኤል 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማቅም ትታጠቃላችሁ፤ ድንጋጤም ይሸፍናችኋል፤ በፊትም ሁሉ ላይ ሐፍረት ይሆናል፤ በራሳችሁም ሁሉ ላይ ቡሃነት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማቅ ይለብሳሉ፤ ሽብርም ይውጣቸዋል። ፊታቸው ኀፍረት ይለብሳል፤ ራሳቸውም ይላጫል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማቅ ይለብሳሉ፥ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በሁሉም ፊቶች ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውም ሁሉ መላጣ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማቅ ይለብሳሉ፤ ድንጋጤ ይይዛቸዋል፤ በፊቶቻቸው ላይ ኀፍረት ይታያል፤ ራሳቸውንም ይላጫሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በፊትም ሁሉ ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውንም ሁሉ ይነጩታል። |
እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
መሥዋዕቱና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት! ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠውያ አገልጋዮች! ዋይ በሉ፤ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።