“አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! ከልባቸው አንቅተው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ፤ ትንቢትም ተናገርባቸው፤
ሕዝቅኤል 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አቅና፤ ትንቢትም ተናገርባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙር፤ ትንቢትም ተናገርባቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርባቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ወደ እስራኤል ተራራዎች ተመልከት፤ በእነርሱም ላይ ትንቢት ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አቅና ትንቢትም ተናገርባቸው። |
“አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! ከልባቸው አንቅተው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ፤ ትንቢትም ተናገርባቸው፤
በሰንሰለትም አስረው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፤ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ ግዞት ቤት አገቡት።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና፤ ወደ መቅደሶችም ተመልከት፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።
እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ስለሚመጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፤ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፤ ሥጋና መንፈስ ሁሉ ይደክማል፤ ከጕልበትም እዥ ይፈስሳል፤ እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ምድሪቱንም ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ፤ የኀይልዋም ስድብ ይቀራል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤ ማንም አያልፍባቸውም።
በመልካም ማሰማርያ አስማራቸዋለሁ፤ ጕረኖአቸውም በረዥሞቹ በእስራኤል ተራሮች ላይ ይሆናል፤ በዚያ በመልካም ጕረኖ ውስጥ ይመሰጋሉ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ ማሰማርያ ይሰማራሉ።
አንተም፦ ፈርሰዋል፤ መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል ብለህ በእስራኤል ተራሮች ላይ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁት ታውቃለህ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው።
በምድርም ላይ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፤ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥት ሆነው አይለያዩም።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።