“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእርሱ በፊት የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵሰት አድርጎአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና፥
ሕዝቅኤል 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኀጢአት ለወጠች፤ በዙሪያዋም ከአሉ ሀገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፤ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከሕዝቦች ይልቅ በትእዛዛቴ ላይ፥ በዙሪያዋ ካሉ አገሮችም ሁሉ ይልቅ በሕጌ ላይ በክፋቷ አምፃለች፥ እነርሱ ትእዛዛቴን አንቀበልም ብለዋልና፥ በሕጌም አልኖሩምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌም ግን ሕጎቼንና ደንቤን በመጣስ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የከፋችና በዙሪያዋም ካሉት አገሮች ይበልጥ እምቢተኛ መሆንዋን አሳይታለች፤ ኢየሩሳሌም ሕጎቼንና ደንቦቼን ንቃለች፤ ትእዛዞቼንም አልተከተለችም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኃጢአት ለወጠች በዙሪያዋም ካሉ አገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፥ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። |
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእርሱ በፊት የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵሰት አድርጎአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና፥
ነገር ግን አልሰሙም፤ እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ክፉ ይሠሩ ዘንድ ምናሴ አሳታቸው።
ነገሥታቶቻችን፥ አለቆቻችንም፥ ካህናቶቻችንም፥ አባቶቻችንም ሕግህን አልጠበቁም፤ ትእዛዝህንና የመሰከርህባቸውን ምስክርህንም አልሰሙም።
በመንግሥትህም በሰጠሃቸው ታላቅ በጎነትህ፥ በፊታቸውም በሰጠሃቸው በሰፊውና በሰባው ምድር አልተገዙልህም፤ ከክፉም ሥራቸው አልተመለሱም።
አሕዛብ፥ “አምላካቸው ወዴት ነው?” እንዳይሉን፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይዩ።
ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፥ ያመልኩአቸውም ዘንድ እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
በትእዛዜ አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አላደረጋችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።”
ሰማርያም የኀጢአትሽን እኩሌታ አልሠራችም፤ አንቺ ግን ከእኅቶችሽ ይልቅ ኀጢአትን አበዛሽ፤ በሠራሽውም ኀጢአት ሁሉ አጸደቅሻቸው።
በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።