ሕዝቅኤል 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፤ እርስዋንና አውራጃዎችዋንም በአሕዛብ መካከል አድርጌአለሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አገሮችን በዙሪያዋ ሁሉ አድርጌ፣ በአሕዛብም መካከል ያስቀመጥኋት ኢየሩሳሌም ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አገሮች በዙሪያዋ ሆነው፥ በመንግሥታት መካከል የተከልዃት ኢየሩሳሌም ይህች ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ኢየሩሳሌምን ተመልከት! ሌሎች አገሮች በዙሪያዋ ሆነው በሕዝቦች መካከል እንድትሆን አድርጌአታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፥ በአሕዛብም መካከል አድርጌአታለሁ፥ አገሮችም በዙሪያዋ አሉ። |
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ ተመልታ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ አሕዛብን ትገዛ የነበረች፥ አውራጃዎችንም ትገዛ የነበረች ገባር ሆናለች።
ባንቺ ላይ ከአኖርኋት ከክብሬ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም ነበረና ስምሽ በአሕዛብ መካከል ተሰማ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከእነርሱም ደግሞ ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላለህ፤ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፤ ከእርስዋም እሳት ይወጣል፤ የእስራኤልንም ቤት ሁሉ እንዲህ ትላቸዋለህ።”
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸውም በኋላቸው ከሚሄደው ከመንፈሳዊ ዐለት የጠጡት ነው፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤
የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስለ አልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደሚአጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።