የጓዳዎቹም መግቢያ ብቻውን ወደሚኖረው ስፍራ ነበረ፤ አንዱ ደጅ ወደ ሰሜን መንገድ፤ አንዱም ደጅ ወደ ደቡብ መንገድ፥ ብቻውን የሚኖረው ስፍራ ወርዱ አምስት ክንድ በዙሪያው ነበር።
ሕዝቅኤል 41:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ፥ በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድርጎ ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ለካ፤ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ነው፤ በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ ግራና ቀኝ ያለው የእያንዳንዱ ክፍል ወርድ አራት ክንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱን ግንብ ስድስት ክንድ፥ በቤቱ ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድርጎ ለካ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው የቤተ መቅደሱን ሕንጻ የውስጠኛ ግንብ ሲለካ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ሆነ፤ ከዚህም ግንብ ጋር ተጠግተው በቤተ መቅደሱ ዙሪያ የተሠሩና የእያንዳንዱ ወርድ አራት ክንድ የሆነ ብዙ ክፍሎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ አድርጎ፥ በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድርጎ ለካ። |
የጓዳዎቹም መግቢያ ብቻውን ወደሚኖረው ስፍራ ነበረ፤ አንዱ ደጅ ወደ ሰሜን መንገድ፤ አንዱም ደጅ ወደ ደቡብ መንገድ፥ ብቻውን የሚኖረው ስፍራ ወርዱ አምስት ክንድ በዙሪያው ነበር።
በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዐይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።