እናንተ የተረፋችሁና መከራ የምትቀበሉ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የነገረኝንና የሰማሁትን ስሙ።
ሕዝቅኤል 40:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ መጥተሃልና በዐይንህ እይ፤ በጆሮህም ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ በልብህ ጠብቅ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐይንህ እይ፤ በጆሮህ ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፤ ወደዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና ያየኸውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዬውም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ ተመርተሃልና በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብህን አድርግ፥ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር አለኝ። |
እናንተ የተረፋችሁና መከራ የምትቀበሉ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የነገረኝንና የሰማሁትን ስሙ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስመረሩኝ ወደ እስራኤል ቤት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ሥራቸውንና ኀጢአታቸውን ይተዉ ዘንድ ለእስራኤል ቤት ይህን ቤት አሳያቸው፤ አምሳያውንም ይለኩ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድርግ፤ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዐትና ሕግ ሁሉ የምነግርህን ሁሉ በዐይንህ ተመልከት፤ በጆሮህም ስማ፤ የቤቱንም መግቢያ፥ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
ከእግዚአብሔር እንደ ተማርሁ አስተምሬአችኋለሁና፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ራሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት ኅብስቱን አነሣ።
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።