እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
ሕዝቅኤል 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ፊትህን ታቀናለህ፤ ክንድህንም ታጸናለህ፤ በእርሷም ትንቢትን ትናገራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ታዞራለህ፣ በዕራቍት ክንድህ ትንቢት ተናገርባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ፊትህን ታዞራለህ፥ ክንድህን ዕራቁቱን አድርገህ ትንቢትን ትናገርባታለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ትኲር ብለህ ተመልከት፤ እጅህንም አንሥተህ የማስጠንቀቂያ ትንቢት በእርስዋ ላይ ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንድህን ዕራቁቱን አድርገህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ክቡ ታቀናለህ፥ ትንቢትም ትናገርባታለህ። |
እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና፤ ወደ መቅደሶችም ተመልከት፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።
የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል ለብረት ቅጥር አድርገው፤ ፊትህንም ወደ እርስዋ አቅና፤ የተከበበችም ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ልጆች ምልክት ይሆናል።
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።