ሕዝቅኤል 32:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በመረቤም አወጣሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ብዙ ሕዝብ ይዤ፣ መረቤን በላይህ ላይ እጥላለሁ፤ በመረቤም ጐትተው ያወጡሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከብዙ ሕዝብ ጉባኤ ጋር ሆኜ መረቤን በላይህ ላይ እዘረጋለሁ፥ እነርሱም በመረቤ ያወጡሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ አሕዛብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በእኔ መረብ መሳቢያም ጐትተው ወደ ዳር እንዲያወጡህ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፥ እነርሱም በመረቤ ያወጡሃል። |
ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች ፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል።
ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ።
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ሆኖም አያያትም፤ በዚያም ይሞታል።
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመድም ይያዛል፤ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፤ በእኔም ላይ ስላደረገው ዐመፅ በዚያ ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።
ሲሄዱም አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም አወርዳቸዋለሁ፤ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ።