እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ሕዝቅኤል 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ጢሮስ ሙሾ አውጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ አድርግ፥ |
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
እነርሱና አባቶቻቸውም በአላወቋቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስከ አጠፋቸውም ድረስ በስተ ኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።
በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፤ እንዲህም ይሉሻል፦ በባሕር የተቀመጥሽ፥ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ የከበርሽ ከተማ ሆይ! እንዴት ጠፋሽ!
“የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሙሽበት፤ እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥበብን የተሞላህ፥ ውበትህም የተፈጸመ መደምደሚያ አንተ ነህ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል።
ስለዚህ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።