La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እን​ዲ​ደ​ርስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ደምን የም​ታ​ፈ​ስሺ፥ እን​ድ​ት​ረ​ክ​ሺም በራ​ስሽ ላይ ጣዖ​ታ​ትን የም​ታ​ደ​ርጊ ከተማ ሆይ!

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በመካከልሽ ደምን በማፍሰስና ጣዖታትን በመሥራት ራስሽን የምታረክሺ፣ ፍርድንም በራስሽ ላይ የምታፈጥኚ ከተማ ሆይ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ ከተማ ሆይ!ጊዜዋ ደርሶአል፥ እንድትረክስም በራስዋ ላይ ጣዖታትን የምታደርግ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ እንዲትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ!

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 22:3
22 Referencias Cruzadas  

ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤


ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


እነ​ርሱ በክፉ መከ​ራና በጭ​ን​ቀት ተሠ​ቃዩ፥ እያ​ነ​ሱም ሄዱ፤


ፍርድ መል​ቶ​ባት የነ​በረ የታ​መ​ነ​ች​ይቱ የጽ​ዮን ከተማ እን​ዴት ጋለ​ሞታ ሆነች! ጽድቅ አድ​ሮ​ባት ነበር፤ አሁን ግን ወን​በ​ዴ​ዎ​ችና ነፍሰ ገዳ​ዮች አሉ​ባት።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የም​ና​ገ​ረ​ውም ቃል ይፈ​ጸ​ማል፤ ደግ​ሞም አይ​ዘ​ገ​ይም፤ እና​ንተ ዐመ​ፀኛ ቤት ሆይ! በዘ​መ​ና​ችሁ ቃሌን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ጽ​መ​ው​ማ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ደም በም​ታ​ፈ​ስስ ከተማ ላይ ትፈ​ር​ዳ​ለ​ህን? ርኵ​ሰ​ቷን ሁሉ አስ​ታ​ው​ቃት።


በው​ስ​ጥዋ ያሉ አለ​ቆ​ችዋ የስ​ስ​ትን ትርፍ ለማ​ግ​ኘት ሲሉ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ፥ ነፍ​ሶ​ች​ንም ያጠፉ ዘንድ እን​ደ​ሚ​ና​ጠቁ ተኵ​ላ​ዎች ናቸው።


ባፈ​ሰ​ስ​ሽው ደም በድ​ለ​ሻል፤ ባደ​ረ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ጣዖ​ታት ረክ​ሰ​ሻል፤ ቀን​ሽ​ንም አቀ​ረ​ብሽ፤ ዘመ​ን​ሽ​ንም አሳ​ጠ​ርሽ፤ ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ መሰ​ደ​ቢያ፥ ለሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ መሳ​ለ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።


“እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አለ​ቆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከዘ​መ​ዶ​ቻ​ቸው ጋር ደም ያፈ​ስሱ ዘንድ በአ​ንቺ ውስጥ ተባ​በሩ።


አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ደምም በእ​ጃ​ቸው አለና፥ ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንም ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ ለእ​ኔም የወ​ለ​ዱ​አ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን መብል እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው በእ​ሳት አሳ​ል​ፈ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና።


ሴቶቹ አመ​ን​ዝ​ሮች ናቸ​ውና፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ደም አለና ጻድ​ቃን ሰዎች በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ቹና በደም አፍ​ሳ​ሾቹ ሴቶች ላይ በሚ​ፈ​ረ​ደው ፍርድ ይፈ​ር​ዱ​ባ​ቸ​ዋል።”


ዝሙ​ቷ​ንም ከተ​መ​ረጡ ከአ​ሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደ​ረ​ገች፤ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸ​ውም ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ረከ​ሰች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?


እር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ቤት ኀጢ​አት እጅግ በዝ​ቶ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም በብዙ አሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች ከተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲሁ ዓመ​ፅ​ንና ርኵ​ሰ​ትን ተሞ​ል​ታ​ለች፤ እነ​ር​ሱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ይም” ብለ​ዋል።


ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም፤ ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።