ሕዝቅኤል 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእስራኤል ልጆች፦ ‘አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ’ ብላችሁ በመካከላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ እስራኤል ምድር፣ “ ‘አባቶች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ የልጆችንም ጥርስ አጠረሰ’ እያላችሁ የምትመስሉት ተምሳሌት ምን ለማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች አጠረሰ፥ ብላችሁ ስለ እስራኤል ምድር የምትመስሉት ምሳሌ ምንድነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእስራኤል ምድር ተደጋግሞ የሚነገር ይህ ምሳሌ ምንድን ነው? ‘ወላጆች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ ነገር ግን የልጆቻቸውን ጥርስ አጠረሰ’ ይላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እስራኤል ምድር፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው? |
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስለ አደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአስቈጡኝ ለእስራኤል ቤት ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፤ ወደ ሀገሩም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
“እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኀጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን በአደረገ፥ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና በአደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በል፦ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ ደስ ብሎሃልና፤
እግዚአብሔርም ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።
እነሆ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፤ ከእርሱም ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ በላቸው።
አባቶቻችሁም በኖሩባት፤ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው፥ የልጅ ልጆቻቸውም ለዘለዓለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘለዓለም አለቃ ይሆናቸዋል።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ በእስራኤል ምድር ላይ መጣ፤ በምድሪቱ በአራቱም ማዕዘን ፍጻሜ መጣ።