እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
ሕዝቅኤል 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? ሥሩም የተነቀለው በብርቱ ክንድና በብዙ ሕዝብ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህም በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያድግ ይሆን? ይጠወልግ ዘንድ ሥሩ ተነቅሎ ፍሬው አይረግፍምን? ቀንበጡም ሁሉ ይደርቃል። ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድና የብዙ ሰው ጕልበት አያስፈልገውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያድግ ይሆንን? እንዲደርቅ፥ አዲስ የበቀለው ቅጠሉም እንዲጠወልግ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አያረግፈውምን? ከሥሩም ለመንቀል ብርቱ ክንድ ወይም ብዙ ሕዝብ አያስፈልገውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ ይህ የተተከለው የወይን ተክል ይጸድቃልን? የመጀመሪያው ንስር ሥሩን ነቅሎ ፍሬው እንዲበሰብስና እንዲደርቅ እንዲሁም ለምለም ቅጠሉ እንዲጠወልግ አያደርገውምን? ሥሩን ለመንቀል ጠንካራ የጦር መሣሪያ ወይም ኀይለኛ ሠራዊት አያስፈልገውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? ሥሩም የተነቀለው በብርቱ ክንድና በብዙ ሕዝብ አይደለም። |
እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኻሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አቷጉ።”
ማልደውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፥ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢዩም እመኑ፤ ነገሩም ይቀናላችኋል” አለ።
ሴዴቅያስም ወደ ባቢሎን ይገባል፤ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከለዳውያን ጋር ብቷጉ ምንም አይቀናችሁም።”
ነገር ግን እናንተን የሚወጉትን የከለዳውያንን ጭፍራ ሁሉ ብትመቱ፤ ከእነርሱም ጥቂት ተወግተው ያልሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያንዳንዱ በስፍራው ይነሣሉ፤ ይህቺንም ሀገር በእሳት ያቃጥላሉ።”
ተተክሎስ፥ እነሆ ይከናወንለት ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።”
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።