እንዳዘዘኝም አደረግሁ፤ ቀን ለቀንም እክቴን እንደ ስደተኛ እክት አወጣሁ፤ በማታም ጊዜ ግንቡን በእጄ ነደልሁ፤ በጨለማም አወጣሁት፤ በፊታቸውም በትከሻዬ ላይ አንግቼ ተሸከምሁት።
ሕዝቅኤል 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ጠዋት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
እንዳዘዘኝም አደረግሁ፤ ቀን ለቀንም እክቴን እንደ ስደተኛ እክት አወጣሁ፤ በማታም ጊዜ ግንቡን በእጄ ነደልሁ፤ በጨለማም አወጣሁት፤ በፊታቸውም በትከሻዬ ላይ አንግቼ ተሸከምሁት።