ሕዝቅኤል 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ከንቱን የሚያስቡ፥ በዚችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ላይ ተንኰልን የሚመክሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ክፉ ምክርን የሚመክሩ ሰዎች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ሰዎች መጥፎ ዕቅድ ያወጣሉ፤ በዚህችም ከተማ ክፉ ምክር ይመክራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያስቡ በዚህችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው። |
ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፤ ኀጢአትንም በኀጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ ከመንፈሴ ዘንድ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፤ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ፍርድ ያውቃሉና።” እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፤ እስራቱንም ቈርጠዋል።
ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፤ ወዮታ በወዮታ ላይ ይከተላል፤ ከነቢዩም ዘንድ ራእይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ሕግ፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።