በራሳቸውም በላይ ከአለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።
ሕዝቅኤል 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመካከልም የአራት እንስሶች አምሳያ ወጣ። መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፤ ሰውም ይመስሉ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእሳቱም ውስጥ የአራት ሕያዋን ፍጡራን አምሳያ ነበረ፤ መልካቸውም የሰው ቅርጽ ይመስል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመካከልም አራት ሕያው ፍጡራን የሚመስሉ ወጡ። መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፥ ሰውም ይመስሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐውሎ ነፋሱም መካከል የሰው መልክ ያላቸው አራት ሕያዋን ፍጥረቶች አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመካከልም የአራት እንስሶች አምሳያ ወጣ። መልካቸውም እንደዚህ ነበረ፥ ሰውም ይመስሉ ነበር። |
በራሳቸውም በላይ ከአለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበረ፤ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ።
የሕይወት መንፈስ በውስጣቸው ነበርና እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፤ እነዚህም ሲበርሩ፥ እነዚያ ከእነርሱ ጋር ይበርሩ ነበር።