ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው ይበርሩ ነበር።
ሕዝቅኤል 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክንፋቸውም በላይ ተዘርግቶ ነበር፤ የእያንዳንዱም ሁለት ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፤ ሁለት ሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ፊታቸው ይህን ይመስል ነበር፤ ክንፋቸውም ወደ ላይ ተዘርግቶ ነበር፤ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ክንፍ ነበራቸው፤ የእያንዳንዱም ክንፍ የሌላውን ክንፍ ይነካ ነበር፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊታቸው እንዲህ ነበረ። ክንፎቻቸውም ወደ ላይ ተዘርግተው ነበር፥ የእያንዳንዳቸውም ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፥ በሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱ እንስሳ ሁለት ክንፎች ወደ ላይ ከፍ ብለው ከእነርሱ ቀጥሎ ያለውን ፍጥረት የክንፎች ጫፍ ይነኩ ነበር፤ የቀሩት ሁለቱ ክንፎቻቸው ግን ተጣጥፈው አካላቸውን ይሸፍኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፋቸውም በላይ ተዘርግቶ ነበር፥ የእያንዳንዱም ሁለት ሁለት ክንፋቸው የተያያዙ ነበሩ፥ ሁለት ሁለቱም ገላቸውን ይከድኑ ነበር። |
ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው ይበርሩ ነበር።
ከጠፈሩም በታች ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተቃንተው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ገላውን የሚከድኑ ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሩት።
ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ተያይዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ይበሩ ዘንድ ክንፋቸውን ከምድር በሚያነሡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የተያያዘ መንኰራኵራቸው አይመለስም ነበር።
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ እኔም እያየሁ ከምድር በረሩ፤ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ነበሩ፤ፊት ለፊት በአለው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በር ዳርቻ ቆሙ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር ከእነርሱ ጋራ በላያቸው ነበረ።