“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
ዘፀአት 36:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳም የወርቅ መያዣዎችን ሠሩ፤ መጋረጃዎችንም አንዱን ከሌላው በመያዣዎች አጋጠሙአቸው፤ አንድ ድንኳንም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠሩ፤ የማደሪያው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድም ተጋጥመው የተሰፉትን ሁለቱን መጋረጃዎች አያያዙባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሠራ፤ መጋረጆችንም እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጠማቸው፤ ማደሪያውም አንድ ወጥ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለቱም በኩል ያሉትን መጋረጃዎች አገጣጥሞ አንድ ለማድረግ ኀምሳ የወርቅ መያዣዎች ሠሩላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳም የወርቅ መያዣዎች ሠሩ፤ መጋረጆችንም እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጠሙአቸው፤ አንድ ማደሪያም ሆነ። |
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።