እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
ዘፀአት 33:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እነሆ፥ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዐለቱም ላይ ትቆማለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በአጠገቤ ስፍራ አለ፤ አንተም በዐለት ላይ ትቆማለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ አለው፦ “እነሆ የምትቆምበት ስፍራ በአጠገቤ አለ፥ በዓለቱ ላይ ትቆማለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እዚህ በአጠገቤ በአለት ላይ የምትቆምበት ስፍራ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዓለቱም ላይ ትቆማለህ፤ |
እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ ስም የሚያስጠራ ቦታን እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምንም እሰጣቸዋለሁ።”
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።
አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድርጌ በምሰጣቸው ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ።
ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ይማፀናል፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማዪቱ ያገቡታል። የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል።