ከእነርሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአገልጋዮችህ ጋር ለመሄድ ና” አለ። ኤልሳዕም፥ “እሽ እኔም እመጣለሁ” አለ።
ዘፀአት 33:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፤ “ሀልዎትህ ከእኛ ጋራ ካልሄደ ከዚህ አትስደደን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንዲህ አለው፦ “አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ ከዚህ አታውጣን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆንክ፥ እኛንም ከዚህ ስፍራ አታውጣን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። |
ከእነርሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአገልጋዮችህ ጋር ለመሄድ ና” አለ። ኤልሳዕም፥ “እሽ እኔም እመጣለሁ” አለ።
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አስገባሃለሁ፤ አንገተ ደንዳና ስለሆኑ ሕዝብህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ ከአንተ ጋር አልወጣም።”
“አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማማነታችንን፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ይቅር በለን፤ ለአንተም እንሆናለን” አለ።
በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው።