ዘፀአት 30:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገበታውንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ መቅረዙንም፥ ዕቃውንም፥ የዕጣን መሠዊያውንም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃዎቹን፣ የዕጣን መሠዊያውን ቅባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገበታውንና ዕቃውን ሁሉ፥ መቅረዙንና ዕቃውን፥ የዕጣን መሠዊያውን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ጠረጴዛውንና በእርሱ ላይ ያሉትን ዕቃዎች፥ መቅረዙንና የእርሱን ማዘጋጃ ዕቃዎች፥ የዕጣን ማዕጠንት ማቅረቢያውን መሠዊያ ትቀባለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገበታውንም ዕቃውንም ሁሉ፥ መቅረዙንም ዕቃውንም፥ የዕጣን መሰዊያውንም፥ |
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም ትቀባበታለህ።