“ለአሮንም ክህነት የታረደውን የአውራውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚለይ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትለየዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።
ዘፀአት 29:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ለክህነት የሆኑትን የአውራውን በግ ብልቶች ቀድሳቸው። የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለክህነት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ድርሻ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። |
“ለአሮንም ክህነት የታረደውን የአውራውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚለይ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትለየዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።
ይህም የተለየ ቍርባን ነውና ከእስራኤልልጆች ዘንድ ለዘለዓለም የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የተለየ ቍርባን ይሆናል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ይሆናል።
የመሥዋዕቱን ወርችና ፍርምባ በእግዚአብሔር ፊት ከሚቀርበው መሥዋዕት የእሳት ቍርባን ከሆነው ስብ ጋር ያመጣሉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ለአንተ፥ ከአንተ ጋርም ለወንዶችና ሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።”
የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል።
የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን፥ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።
ይህም ለእናንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው።
ካህኑም እነዚህን ሁሉ ቍርባን አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ይህም የቍርባን ፍርምባና የመባው ወርች ለካህኑ የተቀደሰ ነው፤ ከዚያም በኋላ ባለስእለቱ ወይን ይጠጣል።
በሬ ወይም በግ ለመሥዋዕት ከሚያቀርቡት ሕዝብ የካህናቱ ወግ ይህ ይሆናል፤ ወርቹንና ሁለቱን ጕንጮቹን፥ ጨጓራውንም ለካህኑ ይሰጣሉ።
ኦሪትስ የሚሞት ሰውን ሊቀ ካህናት አድርጋ ትሾማለች፤ ከኦሪት በኋላ የመጣው የእግዚአብሔር የመሐላ ቃሉ ግን ዘለዓለም የማይለወጥ ፍጹም ወልድን ካህን አድርጎ ሾመልን።
ወጥቤቱም ወርቹን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፥ “ሳኦልን ለምስክር ከባልንጀራህ ተለይቶ ቀርቦልሃልና እነሆ፥ በልተህ የተረፈህን በፊትህ አኑር” አለው። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።