La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 29:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለአሮን ክህነት የአውራ በጉን ፍርምባ ከወሰድህ በኋላ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዘው፤ ይህም የአንተ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለአሮን የክህነት ሥርዓት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለአሮን ክህነት ሥርዓት ከታረደው የበግ አውራ ፍርምባውን ወስደህ ለእኔ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ መባ አድርገህ አንሣ፤ ይህም ለእናንተው የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአሮንም ክህነት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል።

Ver Capítulo



ዘፀአት 29:26
8 Referencias Cruzadas  

ከሚ​ካ​ኑ​በ​ትም አውራ በግ የተ​ወ​ሰደ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ወግ የሚ​ሆን ለመ​ሥ​ዋ​ዕት የተ​ለ​የ​ውን ፍር​ም​ባና የተ​ነ​ሣ​ውን ወርች ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


ካህ​ኑም አን​ዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​የ​ዋል።


የእ​ርሱ እጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳ​ቱን ቍር​ባን ያመ​ጣሉ፤ ፍር​ም​ባ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ በጉ​በቱ ላይ ያለ​ውን መረ​ብና የፍ​ር​ም​ባ​ውን ስብ ያመ​ጣል።


ካህ​ኑም ስቡን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረው፤ ፍር​ም​ባ​ውም ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሁን።


ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ሙሴም ከቅ​ድ​ስ​ናው አውራ በግ ፍር​ም​ባ​ውን ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በው ዘንድ ቈራ​ረጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ይህ ለቅ​ድ​ስና ከታ​ረ​ደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አሮን ፍር​ም​ባ​ዎ​ቹ​ንና ቀኝ ወር​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለየ።