ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
ዘፀአት 29:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፤ በመሥዊያውም ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ እንዲሆን ታቃጥለዋለህ፤ እርሱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከእጃቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋራ ለእግዚአብሔር መልካም መዐዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በጌታ ፊት መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ታቃጥለዋለህ፤ ይህም ለጌታ የእሳት ቁርባን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም በመቀበል ለእኔ የምግብ መባ አድርገህ ታቀርበው ዘንድ በሚቃጠለው መሥዋዕት ጫፍ ላይ አኑረህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ይህም መባ መዓዛው እኔን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በመሠዊያውም ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽቱ እንዲሆን ታቃጥለዋለህ፤ እርሱ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነው። |
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።
ሁለተኛውንም ጠቦት በሠርክ ታቀርበዋለህ፤ እንደ ነግሁም የእህልና የመጠጥ ቍርባን ታደርግበታለህ፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሆናል።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
እግዚአብሔርም እንዲህ አዝዞኛልና፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን ለአንተም፥ ለልጆችህም የተሰጠ ሥርዐት ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ።
“ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት፤ እርሾ ያለበት ነገር፥ ማርም ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና።
ካህኑም ከተፈተገው እህል፥ ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ጋር መታሰቢያውን ያቀርባል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ወደ ካህኑ ወደ አሮን ልጆች ያመጣዋል፤ ከመልካም ስንዴ ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ነጩንም ዕጣን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
ካህኑም ከቍርባኑ መታሰቢያውን ይወስዳል፤ በመሠዊያውም ላይ ይጨምረዋል። ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል ቍርባን ነው።
ከእርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርበዋል፤ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው።
ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርገው ያቀርባሉ፤ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያቀርቡታል፤ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ነው።
ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
ካህኑም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል፤ እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው።
ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አኖረው። በጎ መዓዛ የቅድስና መሥዋዕት ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉድንም በፊቴ ይለብስ ዘንድ፥ የአባትህን ቤት ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የእሳት ቍርባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።