La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 28:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቀሚ​ሱ​ንም ከጥሩ በፍታ ዝን​ጕ​ር​ጕር አድ​ር​ገህ፥ አክ​ሊ​ልን ከበ​ፍታ ትሠ​ራ​ለህ፤ በጥ​ልፍ አሠ​ራ​ርም መታ​ጠ​ቂያ ትሠ​ራ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሸሚዙን ከቀጭን በፍታ ሥራ፤ መጠምጠሚያውንም ከቀጭን በፍታ አብጀው፤ መታጠቂያውንም ጥልፍ ጠላፊ የሠራው ይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እጀ ጠባቡን ከጥሩ በፍታ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፥ በጥልፍ የተጠለፈ መታጠቂያ ትሠራለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሸሚዙንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራር መታጠቂያም ትሠራለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 28:39
10 Referencias Cruzadas  

ለድ​ን​ኳኑ ደጃ​ፍም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ም​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አድ​ር​ግ​ለት።


ለአ​ደ​ባ​ባዩ ደጅም ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀ​ይም ግምጃ ከጥሩ በፍ​ታም በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ ሃያ ክንድ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹም አራት፥ እግ​ሮ​ቹም አራት ይሁኑ።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።


ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት።


አክ​ሊ​ል​ንም በራሱ ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የወ​ር​ቁ​ንም ቀጸላ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ታኖ​ራ​ለህ።


ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሶ​ች​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤


እንደ ሸማኔ ሥራ ከጥሩ በፍታ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እጀ ጠባ​ቦ​ችን፥ ከጥሩ በፍ​ታም አክ​ሊ​ልን፥


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው።


ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።