በታቦቷም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚባሉት ከሁለቱ የድንጋይ ጽላት በቀር ምንም አልነበረባትም።
ዘፀአት 25:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የስርየት መክደኛውን በታቦቱ ዐናት ላይ አስቀምጠው፤ እኔ የምሰጥህን ምስክሩንም በታቦቱ ውስጥ አስቀምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የስርየት መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔ የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታቦቱ ላይ መክደኛውን አድርግ፤ የምሰጥህንም ጽላት በታቦቱ ውስጥ አኑረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። |
በታቦቷም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚባሉት ከሁለቱ የድንጋይ ጽላት በቀር ምንም አልነበረባትም።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ አነገሡትም፤ ኢዮአዳና ልጆቹም አነገሡት፥ “ንጉሡ በሕይወት ይኑር” እያሉም ቀቡት።
ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው።
እንዳይሞትም የጢሱ ደመና በምስክሩ ታቦት ላይ ያለውን መክደኛ ይሸፍን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ያደርጋል።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው በላይ ከኪሩቤልም መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ይናገር ነበር።
ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፤ ጽላቱንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ።