ዘፀአት 21:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ ደኅናውን በሬ ይሽጡ፤ ዋጋውንም በትክክል ይካፈሉ፤ የሞተውንም ደግሞ በትክክል ይካፈሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድለው፣ በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው ገንዘቡንና የሞተውን እንስሳ እኩል ይካፈሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንድ ሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ በሕይወት ያለውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም እኩል ይካፈሉት፤ የሞተውንም ደግሞ እኩል ይካፈሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድል ሁለቱ ሰዎች በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ለሁለት ይካፈሉት፤ የሞተውንም በሬ ሥጋ ለሁለት ይካፈሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው በሬ የሌላውን በሬ እስኪሞት ድረስ ቢወጋ፥ ደኅናውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም በትክክል ይካፈሉ፤ የሞተውንም ደግሞ በትክክል ይካፈሉ። |
በሬውም ትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ ለባለቤቱም ቢመሰክሩለት፥ ባለቤቱም ባያስወግደው በሬውን በበሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።