ዳንኤልም ይህ ሥርዐት እንደ ታዘዘ በዐወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር፤ ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ ከቀኑ በሦስት ሰዓት በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም።