“የማይበድል ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ብትቈጣቸውም፥ ለጠላቶቻቸውም አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላቶቻቸው ቢማርኩአቸው፥
2 ዜና መዋዕል 6:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተማረኩባትም ሀገር ሆነው በልባቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም ሀገር ሳሉ ተመልሰው፦ ኀጢአት ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፉም አድርገናል ብለው ቢለምኑህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጋዙበት አገር ሳሉ ወደ ልቡናቸው ቢመለሱ፣ ንስሓ ቢገቡና በምርኮ ሳሉ፣ ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ ብለው ቢለምኑህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተማረኩበትም አገር ሆነው በልባቸው ንስሐ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም አገር ሳሉ ተመልሰው፦ ‘ኃጢአት ሠርተናል፥ ስሕተት ፈጽመናል፥ ክፉም አድርገናል’ ብለው ቢለምኑህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩበት በዚያች አገር ሳሉ ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ዐምፀናልም’ ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ እግዚአብሔር ሆይ፥ ጸሎታቸውን ስማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተማረኩበትም አገር ሆነው በልባቸው ንስሐ ቢገቡ፥ በምርኮአቸውም አገር ሳሉ ተመልሰው ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለንማል፤ ክፉም አድርገናል፤’ ብለው ቢለምኑህ፥ |
“የማይበድል ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ብትቈጣቸውም፥ ለጠላቶቻቸውም አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላቶቻቸው ቢማርኩአቸው፥
በተማረኩበትም ሀገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው፥ ወደ መረጥሃትም ከተማ፥ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኀጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።