መባኡንና ዐሥራቱን፥ የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡ። ሌዋዊውም ኮክንያስ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤
2 ዜና መዋዕል 35:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዋውያኑም አለቆች ኮኒንያስ በንያስም፥ ወንድሞቹም ሰማዕያስና ናትናኤል፥ ሰብንያስ፥ ኢዮሄል፥ ኢዮዛብድ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችን፥ አምስት መቶም በሬዎችን ለሌዋውያን ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ኮናንያ፣ ወንድሞቹ ሸማያና ናትናኤል እንደዚሁም የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸቢያ፣ ይዔኤልና ዮዛባት ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆኑ ዐምስት ሺሕ በግና ፍየል ዐምስት መቶም በሬ ለሌዋውያኑ ሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌዋውያን አለቆች ኮናንያና ወንድሞቹ የሆኑ ሸማዕያና ነታንኤል እንዲሁም ሐሻብያ፥ ይዒኤልና ዮዛባድ ሌዋውያኑ ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቡአቸውን አምስት ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶችን እንዲሁም አምስት መቶ በሬዎችን ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ። |
መባኡንና ዐሥራቱን፥ የተቀደሱትንም በእምነት ወደዚያ አገቡ። ሌዋዊውም ኮክንያስ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤