ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤዎችን ጻፈ።
2 ዜና መዋዕል 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴንና የኤፍሬምንም፥ የስምዖንና የንፍታሌምንም ከተሞች፥ በዙሪያቸውም ያለውን ቦታ እንዲሁ አነጻ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ንፍታሌም ባሉ በምናሴ፣ በኤፍሬምና በስምዖን ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ባሉ የፈራረሱ አካባቢዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናሴንና የኤፍሬምንም የስምዖንና የንፍታሌምንም ከተሞች፥ በዙሪያቸውም ያለውን ቦታ እንዲሁ አነጻ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ሰሜን ንፍታሌም ድረስ ባሉ በምናሴ፥ በኤፍሬምና በስምዖን ግዛቶች በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በተደመሰሱት አካባቢዎቻቸው ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴንና የኤፍሬምንም፥ የስምዖንና የንፍታሌምንም ከተሞች፥ በዙሪያቸውም ያለውን ቦታ እንዲሁ አነጻ። |
ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤዎችን ጻፈ።
ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በይሁዳ ከተሞች የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወጥተው ዐምዶቹን ሰበሩ፤ ዐፀዶችንም ኮረብታዎችንም አፈረሱ፤ መሠዊያውንም አጠፉ። በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን ፈጽመው እስከ ዘለዓለሙ አጠፉአቸው። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል።