የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
2 ዜና መዋዕል 34:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህኖቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። ይሁዳንና ኢየሩሳሌምንም አነጻ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናቱን ዐጥንት በመሠዊያዎቻቸው ላይ አቃጠለ፤ በዚህ ዐይነትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናቶቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ፤ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስያስ የአሕዛብን ካህናት ዐፅም ሁሉ እነርሱ ራሳቸው ይሰግዱላቸው በነበሩት መሠዊያዎች ላይ አቃጠላቸው፤ ይህን ሁሉ በማድረጉም ይሁዳና ኢየሩሳሌም በሥርዓት እንደገና እንዲነጹ አደረገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናቶቻቸውንም አጥንት በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ፤ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። |
የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
ኢዮስያስም ዘወር ብሎ በከተማው የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ኢዮርብዓምም በበዓል ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ ልኮ ከመቃብሮቹ አጥንቶቹን አስወጣ፥ በመሠዊያው ላይም አቃጠላቸው፥ አረከሰውም። ዘወርም ብሎ ይህን ቃል ወደ ተናገረው ወደ እግዚአብሔር ሰው መቃብር ዐይኖቹን አቀና። እንዲህም አለ፦
በዚያም የነበሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ካህናት ሁሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ገደላቸው፥ የሰዎቹንም አጥንት በመሠዊያዎቹ ላይ አቃጠለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ኢዮስያስም ከእስራኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩሱን ሁሉ አስወገደ፤ በእስራኤልም የተገኙትን ሁሉ አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረገ። በዘመኑ ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል አልራቁም።
መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎችም አደቀቀ፤ በእስራኤልም ሀገር ሁሉ የኮረብታዎችን መስገጃዎችአጠፋ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ምድርን የሚያረክሳት ደም ነውና የምትኖሩባትን ምድር በነፍስ ግድያ አታርክሷት። ምድሪቱም በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።