ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
2 ዜና መዋዕል 33:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዘዝኋቸውንም ሁሉ፥ በሙሴ የተሰጠውን ሕግና ሥርዐት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደ ገና አላርቅም” ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሠራውን ጣዖትና የተቀረጸውን ምስል አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴ አማካይነት ያዘዝኋቸውን ሕጎቼን፣ ደንቦቼንና ሥርዐቶቼን ሁሉ በጥንቃቄ ይፈጽሙ እንጂ፣ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር ለቅቆ እንዲወጣ አላደርግም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “እኔ ያዘዝኋቸውን ሁሉ፥ በሙሴም በኩል የተሰጠውን ሕግና ሥርዓት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር እስራኤል እንደገና እንዲሰደዱ አላደርግም” ብሎ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በሙሴ አማካይነት ያዘዝኳቸውን ሕጌን፥ ሥርዓቴንና ድንጋጌዬን ሁሉ በጥንቃቄ ቢጠብቁ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር እንደገና እንዲፈናቀሉ አላደርግም። |
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ የኀጢአትም ልጆች እንደ ቀድሞው አያስጨንቁትም፤
ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ አላቸው፥ “እስራኤል ሆይ እንድትማሩአትም፥ በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድርጌ በምሰጣቸው ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ።
“በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት፥ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።