ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
2 ዜና መዋዕል 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም በተመሰገነው ስምህ ነው፤ ኀይልህ ከመገለጡ የተነሣ ሁሉ የሚርድና የሚንቀጠቀጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔርን መሠዊያ ዐደሰ፤ በላዩም የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መሥዋዕት አቀረበ፤ ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታንም መሠዊያ ደግሞ አደሰ፥ የአንድነትንና የምስጋናንም መሥዋዕት ሠዋበት፤ ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ ጌታን እንዲያገለግሉ አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርንም መሠዊያ በማደስ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕትና የምስጋና መባን አቀረበ፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያመልኩም ዘንድ መላውን የይሁዳ ሕዝብ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም መሠዊያ ደግሞ አደሰ፤ የደኅንነትንና የምስጋናንም መሥዋዕት ሠዋበት፤ ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አዘዘ። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
የእንግዶቹንም አማልክት መሠዊያ፥ የኮረብታውንም መስገጃዎች አፈረሰ፤ ሐውልቶቹንም ሰበረ፤ የማምለኪያ አፀዶቹንም ቈረጠ፤
ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው፥ “የእግዚአብሔርን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የኅብስተ ገጹንም ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤
ሕዝቅያስም፥ “አሁን እጃችሁን ለእግዚአብሔር አንጽታችሁ ቅረቡ፤ መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተናገረ። ጉባኤውም መሥዋዕቱንና የምስጋናውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጡ፤ ልባቸውም የፈቀደ ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አመጡ።
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።