እግዚአብሔርም እንደ ተመለሱና እንደ ተፀፀቱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፥ “ከተመለሱ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።
2 ዜና መዋዕል 33:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተጨነቀም ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ፈለገ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ሰውነቱን እጅግ አዋረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨነቀም ጊዜ የአምላኩን የእግዚአብሔርን በጎነት ፈለገ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተጨነቀም ጊዜ አምላኩን ጌታን ፈለገ፥ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ ሥቃይ በበዛበት ጊዜ ራሱን በትሕትና በማዋረድ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርንም ርዳታ ለመነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተጨነቀም ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ፈለገ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ሰውነቱን እጅግ አዋረደ፤ |
እግዚአብሔርም እንደ ተመለሱና እንደ ተፀፀቱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፥ “ከተመለሱ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።
እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር በሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም መታው፤ ከእርሱም ብዙ ምርኮኞችን ወሰደ፤ ወደ ደማስቆም አመጣው። ደግሞም በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም በታላቅ አመታት መታው።
ሕዝቅያስም በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቅያስ ዘመን ቍጣውን አላመጣባቸውም።
በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራ በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ፤ ከትልልቆች ጋር፥ ከእኔም ይልቅ ከሚከብሩ ጋር አልሄድሁም።
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትደርስ ይሆናል፤ ሁሉም ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”
ጌታም፥ “ተነሣና ቅን በምትባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ከጠርሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸልያልና” አለው።