ወንድሞቻቸውንም ሰብስበው በእግዚአብሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእዛዝ የእግዚአብሔርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳቸውን አነጹ።
2 ዜና መዋዕል 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ተዘጋጁ ነጹም። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን በግ ዐረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ ዐፍረው ስለ ነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦት አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አዋረዱ፥ ተቀደሱም፥ ወደ ጌታም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ፤ ካህናቱና ሌዋውያኑም አፈሩ፤ ተቀደሱም፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ። |
ወንድሞቻቸውንም ሰብስበው በእግዚአብሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእዛዝ የእግዚአብሔርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳቸውን አነጹ።
ጉባኤውም ያመጡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቍጥር ሰባ ወይፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
ነገር ግን ካህናቱ ጥቂቶች ነበሩና የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ አይችሉም ነበር፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር።
ንጉሡ ሕዝቅያስም ስለ ቍርባን ሺህ ወይፈኖችንና ሰባት ሺህ በጎችን ለይሁዳና ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለቆቹም ሺህ ወይፈኖችንና ዐሥር ሺህ በጎችን ለጉባኤው ሰጥተው ነበር፤ ከካህናቱ እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና።
ካህናቱ በሚበቃ ቍጥር ስላልተቀደሱ፥ ሕዝቡም ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰቡ በጊዜው ያደርጉት ዘንድ አልቻሉም ነበርና።
በማኅበራቸውም ሁሉ በየትውልዳቸው ለተቈጠሩ ለሚስቶቻቸው፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸውም ይሰጡ ነበር፤ በእምነት ፈጽመው ተቀድሰዋልና።
የፋሲካውንም በግ እረዱ፤ እናንተም ተቀደሱ፥ እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ የተናገረውን ቃል ታደርጉ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።”
ካህናቱና ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር፤ ሁሉም ንጹሓን ነበሩ፤ ለምርኮኞቹም ልጆች ሁሉ፥ ለወንድሞቻቸው ለካህናቱ፥ ለራሳቸውም የፋሲካውን በግ ዐረዱ።