በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
2 ዜና መዋዕል 29:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው፥ “የእግዚአብሔርን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የኅብስተ ገጹንም ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉ፤ “የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሙሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ ከነዕቃዎቹ ሁሉ፣ ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን ጠረጴዛ፣ ከነዕቃዎቹ አንጽተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉት፦ “የጌታን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የተቀደሰውም ሕብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያኑ ስለ ተከናወነው ሥራ ለንጉሥ ሕዝቅያስ የሚከተለውን መግለጫ አቀረቡ፦ “የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የተቀደሰው ኅብስት የሚቀመጥበትን ገበታና ከእነርሱም ጋር የተያያዙትን ሌሎች ዕቃዎች ጭምር ቤተ መቅደሱን በሙሉ አንጽተናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ውስጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው “የእግዚአብሔርን ቤት ሁሉ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያና ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ሕብስት ገበታና ዕቃውን ሁሉ አንጽተናል፤ |
በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
በመጀመሪያውም ወር በመጀመሪያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚያውም ወር በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በስምንት ቀን አነጹ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ፈጸሙ።
ንጉሡም አካዝ ነግሦ ሳለ በመተላለፉ ያረከሰውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅተናል፤ ቀድሰናልም፤ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ሆነዋል” አሉት።