La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አካ​ዝም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከን​ጉ​ሡና ከአ​ለ​ቆ​ቹም ቤት የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠ፥ ነገር ግን አስ​ጨ​ነ​ቀው እንጂ አል​ረ​ዳ​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካዝም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ከቤተ መንግሥቱና ከመሳፍንቱ ዕቃዎች ዘርፎ ለአሦር ንጉሥ ሰጥቶት ነበር፤ ነገር ግን አልረዳውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አካዝም ከጌታ ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኩሌታውን ገፈፈ፥ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን እንዲህ ማድረጉ አንዳች አልጠቀመውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ አካዝ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ ከቤተ መንግሥቱና ከሕዝቡ መሪዎች ዘንድ ብዙ ወርቅ ወስዶ ለንጉሠ ነገሥቱ መማለጃ አድርጎ ሰጠ፤ ይሁን እንጂ ይህን ማድረጉም አልጠቀመውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አካዝም ከእግዚአብሔር ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኵሌታውን ገፈፈ፤ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን አንዳች አልተጠቀመበትም።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 28:21
8 Referencias Cruzadas  

የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ወሰደ፤ ሁሉ​ንም ወሰደ፤ ደግ​ሞም ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ዎ​ችን ወሰደ።


አሳም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ከን​ጉሥ ቤት መዝ​ገብ ብርና ወርቅ ወስዶ፦ በደ​ማ​ስቆ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ሶርያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር ላከ። እን​ዲ​ህም አለው፦


ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል።


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።