በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
2 ዜና መዋዕል 28:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ አስጨነቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ እርሱ መጥቶ ነበር፤ ሆኖም ችግር ፈጠረበት እንጂ አልረዳውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴርም አካዝን በመርዳት ፈንታ ተቃወመው፤ ችግርም አመጣበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም። |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፋሎክን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።
እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልእክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥነው ሄዱ፥ “የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ ያዕቆብም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
ነገር ግን፥ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፤ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ ባመጣው ታላቅ ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።
እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
ኤፍሬምም ደዌውን አያት፤ ይሁዳም ሥቃዩን አያት፤ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈውሳችሁ ዘንድ አልቻለም፤ ከእናንተም ሕማም አልተወገደም።